የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ ሰጠ

85

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ መስጠቱን አስታወቀ ።

በጥናትና ምርምር ስራቸው የላቀ የፈጠራ ውጤት ላስመዘገቡት አራት ውጤታማ መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ ከመጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስጠቱን የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አረጋግጧል ።

ከአውቶሞቲቭ ምህንድስና ዘርፍ ሌተናል ኮሎኔል ዶክተር ብስራት የሱፍ፣ ከሜካኒካል ዲዛይን ሻለቃ ዶክተር ሰሎሞን ሰይድ፣ ከኬሚካል ምህንድስና ሻለቃ ዶክተር ወንዳለም ምስጋነውና ከሜካትሮኒክ ምህንድስና ሻለቃ ዶክተር ርእሶም ወልደ ጊወርጊስ ናቸው የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረጉን ያገኙት።

መምህራኑ በየስራ ዘርፋቸው ባስመዘገቡት ልዩ ውጤት የተመዘኑ መሆኑም ተገልጿል።

በወታደራዊ አገልግሎት ስራ ላይ ለሚገኙ ምሁራን የተሰጠው የደረጃ እድገት በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገውም ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም