የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ጄን ቻርልስ ካራምባን ጋር ተወያዩ

237

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ጄን ቻርልስ ካራምባንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸው በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ ጉዳዮች እና ከአሁን በፊት ሁለቱ ሀገራት በትብብር የሚሰሩባቸውን ጉዳዮች ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ሩዋንዳ በኪጋሊ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሠራበት ቦታ መስጠቷም ለግንኙነቱ መጠናከር አንዱ ማሳያ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል።

ሁለቱ አካላት በቀጣይ በአዲስ አበባ እና ኪጋሊ ከተሞች ያለውን እህትማማችነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይም መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም