ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄን አስጀመሩ 

265

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄን በአዲስ አበባ ዛሬ አስጀመሩ።  

ንቅናቄው "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ኃሳብ ለቀጣይ ስድስት ወራት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የክልል የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊዎችና የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል። 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የተጠናከረ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች።


 

በዚህም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን ጨምሮ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ ከተሞችን ውብና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል። 

ዛሬ የተጀመረው አገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል እንደሚሰራ ገልጸው በዘርፉ የተጀመሩ ጥረቶችን ያጠናክራል ብለዋል።  

ንቅናቄው ከተሞች የሚያስወግዱትን ቆሻሻ በአግባቡ ሥርዓትን የተከተለ በማድረግ ውብና ምቹ ከተማ ለመገንባት ያለመ መሆኑም ተመላክቷል። 

የደምጽ ብክለትን መከላከልም ሌላው ንቅናቄው የሚሰራበት ዘርፍ መሆኑም እንዲሁ።  

የአየር፣ የውኃ፣  የአፈርና የድምፅ  ብክለቶች ለመቀነስ ማኅበረሰቡን በማሳተፍ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም