በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የብልጽግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በአዳማ እየተካሔደ ነው

160

አዳማ፤ መጋቢት 20/2016 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በአዳማ ከተማ አባገዳ አደራሽ መካሄድ ጀመረ።


 

በኮንፈረንሱ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከፓርቲው የተወከሉ አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም