በመላ ሀገሪቱ የተቋረጠው ኃይል መልሶ መገናኘት ጀምሯል

140

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016 (ኢዜአ)፦ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ መገናኘት ጀምሯል።

በዚህም መሰረት አብዛኛው የአዲስ አበባ ክፍል እና የተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች መልሰው ኃይል ማግኘት ችለዋል።

የተቀሩትን አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ጥረቱ ቀጥሏል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም