የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ እየተከናወነ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል

113

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ)፦ የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ።

ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል የተቋረጠ ሲሆን ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ሲል ገልጿል።

የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ ሲሆን ችግሩን በመቅረፍ ዳግም ሲስተሙ እስከሚገናኝ ድረስ ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም