በጅቡቲ ትላንት ሌሊት በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ደረሰ

403

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ)፦በጅቡቲ ትላንት መጋቢት 18/07/2016ዓ.ም ለሊት በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ መድረሱ ተገለጸ።

በተለይም በልበላ በተባለው አካባቢ የደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ዝርዝር የጉዳቱን መጠን ለማጣራት ጥረት እየተደረገም ይገኛል።


 

የጅቡቲ አየር ሀይል እና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ክፍል ሰራተኞች በሂሊኮፕተር ጭምር በመታገዘ በጎርፍ አደጋ የገጠማቸውን ሰዎች በመርዳት ላይ እንደሚገኙ የኢዜአ ምንጮች ገልጸዋል።

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም