የአማራ ክልልን ሰላምና ዕድገት ለማስቀጠል ርብርብ እንደሚደረግ ተገለጸ

153

ደብረብርሃን፣ መጋቢት 19 ቀን 2016 (ኢዜአ)፡- ፈተናዎችን በመሻገር የክልሉን ህዝብ ሰላምና ዕድገት ለማስቀጠል ርብርብ በማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ በአማራ ክልል  የሰሜን ሸዋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ አባላት ገለጹ። 

አባላቱ በክልላዊና ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በደብረብርሃን ከተማ የምክክር መድረክ አካሄደዋል።

ከተሳታፊዎቹ መካከል አቶ ዳዊት ዳምጠው በሰጡት አስተያየት ከምክክር መድረኩ የሚሰጡትን ተልዕኮዎች  በብቃት ለመፈጸም የሚያበቃቸውን  ግንዛቤ  መጨበጣቸውን አመልክተዋል፡፡

በዚህም በተለይ  የክልሉን ሰላም፣ ልማትና እድገት ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ሌላው አባል አቶ አማረ ጅማ ፤ በፓርቲ እስካሁን በተከናወኑ ስራዎች ላይ ሰነድ ቀርቦ በመድረኩ ምክክር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ባሳለፍናቸው ጊዜያት ክልሉን ብሎም ሀገሪቱን ሊያሻግሩ የሚችሉ ሁሉን አቀፍ የልማትና የመልካም አስተዳደር  ስራዎችን በትኩረት ሲሰራ እንደቆየ መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።

ፓርቲው በቀጣይ  ለሚያከናውናቸው  ሁሉን አቀፍ ስራዎች እንዲሳኩ ፣ፈተናዎችን በመሻገር  የክልሉ ሰላምና ዕድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።

በፅንፈኛው የተፈጠረውን ችግር ከመቀልበስ ጎን ለጎን  የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማትና የሰላም፣ የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የተናገሩት ደግሞ በሰሜን ሸዋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ ሰዓዳ ኢብራሂም ናቸው።

የምክክር መድረኩ የአባላቱን አቅም በማጎልበት የህዝቡን  ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚና ማህበራዊ  ዕድገቶችን ለማስመዝገብ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል።

በየተሰማራንበት የስራ መስክ ብልሹ አሰራርና ሙስናን በመታገል ብሎም  ታማኝ የህዝብ አገልጋይ በመሆንም የኢትዮጵያን ህብረ ብሄራዊነትን ለማስጠበቅ መረባረብ አለብን ሲሉም አሳስበዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም