ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአቅመ ደካሞችና ሀገር ባለውለታዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

167

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ):- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለልማት ከሚኖሩበት አካባቢ ለተነሱ ነዋሪዎች ለአቅመ ደካሞችና የሃገር ባለውለታዎች የመኖሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።

የቤቶቹ የግንባታ መሰረት ድንጋይ የተቀመጠው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ አካባቢ ነው።


 

የሚገነቡት ባለ አምስት ወለል ሶስት ዘመናዊ ህንፃዎች ሲሆን በድምሩ 108 መኖሪያ ቤቶች ያሉት መሆኑ ተገልጿል።

የህንጻዎቹ ግንባታ በባለሃብቶች ድጋፍ የሚከናወንና በ90 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም