አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከአሜሪካ የቆንስላ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ሪና ቢይተር ጋር ተወያዩ

128

አዲስ አበባ ፤መጋቢት 19/2016 (ኢዜአ):- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከአሜሪካ የቆንስላ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ሪና ቢይተር ጋር  ተወያይተዋል። 

ውይይቱ በቆንስላ አገልግሎት ጉዳዮች፣ በቪዛ አሰጣጥ እና ለሁለቱ ሀገራት  ዜጎች በሚሰጡ መሰል አገልግሎቶች ዙሪያ  ላይ ያተኮረ ነው።

በቀጣይ በቆንስላ አገልግሎት እና  ቪዛ አሰጣጥ ዙሪያ   የበለጠ  በትብብር ለመስራት  መስማማታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም