የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን የሰጠው ግብረ-መልስ በስራ ላይ ይውላል - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

132

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2016(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የሱፐርቪዥን ስራ ሲያካሒድ የቆየው የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን የሰጠው ግብረ-መልስ በስራ ላይ እንደሚውል የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተመራው የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በክልሉ ሲያካሒድ የቆየው ሱፐርቪዥን መጠናቀቁን አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።

ቡድኑ በክልሉ ያካሔደውን የሱፐርቪዥን ስራ ተከትሎም ግብረ-መልስ ሰጥቷል።

የክልላችን መንግስት የተሰጠውን ግብረ-መልስ እንደግብአት ወስዶ በስራ ላይ የሚያውል መሆኑን እየገለፅኩ ቡድኑን በራሴና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስም ላመሰግን እወዳለሁ ማለታቸውን ከማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም