በሸኔ ቡድን ላይ እየተወሠደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል

197

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2016(ኢዜአ)፦ በሸኔ ቡድን ላይ እየተወሠደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ።

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ዳሌ ዳክን ጨምሮ በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ህብረተሠቡን ሠላም ሲያሳጣ በነበረው የሸኔ ቡድን ላይ በቀጣናው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት አሥፈላጊውን እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

ሠራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት በሸኔ የሽብር ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ የሸኔ ቡድን ታጣቂ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።


 

በተለያየ አጋጣሚ የሠላም ሃሳብ ሲቀርብለት ለመቀበል ወደ ኋላ የሚለውና ህዝብን እያሥገደደ የሚዘርፈው የሸኔ ቡድን በተለያዩ ቦታዎች በመከላከያ ሠራዊቱ እየተወሠደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ተስኖት እየተበታተነ መሆኑም ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ብቻ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ዳሌ ዳክንና አካባቢው በቀጠናው የሚገኘው ሠራዊት በሸኔ ቡድን ላይ በወሠደው እርምጃ 12 ታጣቂ ተማረኮ 2 የተደመሱ ሲሆን 8 ክላሽ፣ 2 ብሬን እና 3 ኋላ ቀር መሳሪያም መማረኩን አስታውቋል።

በሽብር ቡድኑ ላይ የሚወሰደው ዘመቻ የቀጠለ መሆኑን ከሥፈራው የሚገኙ የሠራዊቱ አመራር መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም