ቀጥታ፡

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2016(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ አራተኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።


 

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት አማካሪና የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ-ግብር የበላይ አስተባባሪ ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ በዚሁ ጊዜ፤ ረመዳን የመሰባሰቢያና የአብሮነት ወር ነው ብለዋል።

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር አንድነትን የሚንጸባረቅበት፣ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት እንዲሁም አብሮነትን የበለጠ የሚጎላበት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም