በአሸባሪው የሸኔ ቡድን ላይ በተወሰደው እርምጃ በርካታ የቡድኑ አባላት መማረካቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2016(ኢዜአ)፦በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ላይ የምዕራብ ዕዝ ሰራዊት በአሸባሪው ሽኔ ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ የቡድኑ አባላት መማረካቸው ተገልጿል።

የኮሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሀብታሙ ምህረቴ በቀጣናው በተለያየ ቦታ የኮሩ ሰራዊት በወሰደው የማጥራት ዘመቻ ከሽብር ቡድኑ የተማረኩ አባላት አብዛኛው ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ ይህ የሽብር ቡድን አሁን ያለው አደረጃጀት እየፈረሰ በመምጣቱ ህፃናትና ሴቶችን ማስገደድና ለሽብር ተግባር ማሰማራቱን ገልፀዋል።

የኮሩ ሠራዊት በየትኛውም አስቸጋሪ ቀጣና በመግባትና ክፍሎች ከክፍሎች በመተሳሰር በሽብር ቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን ገልፀው የህዝብ ተመራጭ የሆኑት የመስተዳድር አካላት በተረጋጋና በተመቻቸ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገም ይገኛል ብለዋል።


 

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የአስራ ሁለት አመት ህፃን የሆነው ያሲን ኢብራሂም እና የአስራ ሰባት ዓመት ወጣት የሆነችው ጫልቱ ከድር የአሸባሪው የሸኔ ቡድን በአካባቢው ለኦሮሞ ነፃነት ታገሉ በማለት አስገድዶን በየበርሃው እያንከራተን ዝርፊያና ግድያ ውስጥ እንድንሰማራ አድርጎናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም