ኢትዮጵያ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸነፈች

295

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2016(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

ጎሎቹን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቸርነት ጉግሳ እና ከነዓን ማርክነህ ከእረፍት መልስ አስቆጥረዋል፡፡

ለሌሴቶ ብቸኛዋን ግብ ሌህሎሆኖሎ ፎቶአኔ ማስቆጠሩን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም