"ስለ እናት ምድር" ፊልም ተመረቀ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2016(ኢዜአ)፦ "ስለ እናት ምድር" የተሰኘ ትኩረቱን በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረገ ፊልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ተመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


 

ፊልሙ በሀገር ፍቅርና በሰራዊቱ ህይወት ላይ ያተኮረ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት በተለይ በሰሜኑ ጦርነት ለአገር ሉአላዊነት መጠበቅ የከፈለውን አይተኬ ዋጋ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ በተዘጋጀው “ስለ እናት ምድር” ፊልም ላይ 30ሺ ሰዎች ተሳትፈዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም