ቀጥታ፡

የአድዋ ድል ለሰራዊቱ አባላት ጀግንነትን፣ አንድነትንና ፈተናን በጽናት መሻገርን ያወረሰ ድል ነው- የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት

አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 11/2016(ኢዜአ)፦  የአድዋ ድል ለሰራዊቱ አባላት ጀግንነትን፣ አንድነትንና ፈተናን በጽናት መሻገርን ያወረሰ ድል  መሆኑን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ተናገሩ።

 የአድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኙ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አመራሮችና አባላት የአድዋ ድልን በልኩ የሚያሳይ መታሰቢያ መገንባቱ ለሰራዊቱ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል።

የጎብኚዎቹ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት ኮሎኔል መኳንንት ደሳለኝ ለኢዜአ እንዳሉት የአድዋ ድል ከኢትዮጵያ ባሻገር የመላው ጥቁሮች ድልና ኩራት መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት ድሉን በቅጡ የሚወክል ተቋም እንዳልነበር ጠቅሰው፤ ድሉን የሚዘክር መታሰቢያ መገንባቱ የአድዋን ታሪክ በቅጡ ለመዘከርና ለትውልድ ለማሻገር እንደሚበጅ አስረድተዋል።

ድሉ ለአየር ኃይል አባላት ጀግንነትን፣ አንድነትን፣ የሀገር ፍቅር እና ፈተናን በጽናት የመሻገር ቁርጠኝነት ያወረሰ እንደሆነም ገልጸዋል።

በዚሁ ወቅት የሰራዊቱ አባላት ከአድዋ አባቶች የወረሷቸውን እሴቶች በማጎልበት ሀገራቸውን ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር እንደሚተጉ አረጋግጠዋል።


 

በተመሳሳይ ሲኒየር ቴክኒሻን ቢልጥማ በሬ፣ ሻምበል እህትነሽ ማርሸትና ምክትል መቶ አለቃ ኤፍሬም ማሬ የአድዋ አባቶች በአንድነትና በጽናት ሀገራቸውን ላለማስደፈር የተዋደቁበት አኩሪ ታሪክ መሆኑን ጠቅሰዋል።


 

አድዋ የድልና የነጻነት ዓርማ እንደሆነ ያነሱት አባላቱ፤ ድሉንና የድሉ ባለቤት የሆኑ አባቶችን የሚዘክር ተቋም መገንባቱ ሀገራቸውን በቁርጠኝነት ለማገልገል እንዳነሳሳቸው ነው የጠቀሱት።

የሰራዊቱ አባላት ከአድዋ ድል በርካታ እሴቶችን መውረሳቸውንና ሀገራቸውን ለማገልግል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።


 

እንደ አየር ኃይል ዘመኑ የደረሰበትን ስንቅና ትጥቅ በማሟላት በአቪየሽን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ዋልታና መከታ የሆነ ተቋም እየተገነባ መሆኑንም አንስተዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም