ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሥራ ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን አመሰገኑ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሥራ ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን አመሰገኑ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2016(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሥራ ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን አመስግነዋል።
የዓለም ባንክ ላለፉት አመታት ለኢትዮጵያ ላደረገው ያላሰለሰ ድጋፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማመስገናቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያሰፈሩት መረጃ ያመላክታል።