ቀጥታ፡

አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ ይገባል - የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝዳንት

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2016(ኢዜአ)፦ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጣሰው ገብሬ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ -ግብሩ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም ወደ ኋላ የማይመለስ እርቅ እንዲፈጠር የወንጌል አማኞች የሚጸልዩበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡


 

አክለውም መርሐ -ግብሩ ምዕመኑ ለሀገሪቱ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ "ጌታ እንዲረዳው" የሚማልድበት መሆኑን ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስር ያሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ አባቶች፣ ዘማሪያን፣ መጋቢዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም