ቀጥታ፡

ለሀገር ሰላምና አንድነት የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2016(ኢዜአ)፦ ለሀገር ሰላምና አንድነት የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ካውንስል የተዘጋጀ ነው።

በዚህም መሰረት በርካታ የእምነቱ ተከታዮች የታደሙበት የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል።


 

የጸሎትና ምስጋና ስነ ስርአቱ በተለይም ስለ ሰው ልጆች ሁሉ ሰላም፤ የሀገር ሰላምና አንድነትን በተመለከተ በፀሎትና ዝማሬ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ካውንስል ስር ያሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ አባቶች፣ ዘማሪያን፣ መጋቢዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም