በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ከ100 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል - ኢዜአ አማርኛ
በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ከ100 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2016(ኢዜአ)፦ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው 12 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ከ100 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ ተገለጸ።
የስራ እድሉ ከተፈጠረላቸው ዜጎች መካከል ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውም ተጠቅሷል።
የስራ እድል ፈጠራው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደ ሀገር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የሚታይ ውጤት እያመጡ መሆኑም ተመላክቷል።
ኮርፖሬሽኑ አሁንም ወደ ስራ የሚያስገባቸው ኢንቨስትመንቶች ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል።