ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ የሚያከናውኑት የፀሎት ፕሮግራም የተወሰኑ መንገዶች ለተሸከርካሪ ዝግ ይሆናሉ - የአዲስ አበባ ፖሊስ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ የሚያከናውኑት የፀሎት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶችን ለተሸከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አሽከርካሪዎች እንደተለመደው ለትራፊክ ፖሊሶች ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑም ጠይቋል፡፡ 
         
በዚህም ዕሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የፀሎት መርሐ-ግብሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ብሏል፡፡

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑም ነው ፖሊስ ጥሪውን ያስተላለፈው፡፡

በዚህም መሰረት ፦  

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ 

• ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

• የቀድሞው አራተኛ ክፍለ ጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ) 

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ
 
• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ 

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

ዕሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ብሏል፡፡ 

ፕሮግራሙ በሚከናወንበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም