ንግድ ባንክ የውስጥ ሲስተም ችግር እንጂ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት አስታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
ንግድ ባንክ የውስጥ ሲስተም ችግር እንጂ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት አስታወቀ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 07/2016 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውስጥ ሲስተም ችግር እንጂ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት አስታወቀ፡፡
ባንኩ ተቋርጦ የነበረውን የኤ ቲ ኤም አገልግሎትሥራ ያስጀመረ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቋል፡፡
ባንኩ የተከሰተው የአገልግሎት መቋረጥ በባንንኩ የውስጥ የሲስተም ችግር እንጂ ፣ በሀሰት እንደሚሰራጨው ከባንኩ ውጭ በደረሰ የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አለመሆኑን ገልጾ፤ ባንኩ አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ያለው መሆኑንም ነው ያስገነዘበው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ደንበኞች ምንም ዓይነት ስጋት እንዳይገባቸው አሳስቦ ችግሩን በሰዓታት ልዩነት ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡