ቀጥታ፡

በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2016 (ኢዜአ) በሲስተም ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለጸ፡፡

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም ገልጿል፡፡

ባንኩ በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት የጀመረ መሆኑን ለደምበኞቹ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን (ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር) ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ባንኩ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም