ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ምክንያት የተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማስጀመር እየሰራ  መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7/2016 (ኢዜአ) በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ የተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  አስታውቋል።

በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ ማጋጠሙን የገለጸው ባንኩ፤ አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር እየሰራ  መሆኑን ገልጿል።

ባንኩ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም