ቀጥታ፡

ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ መርኃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2016(ኢዜአ)፡- በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ (ኮምፖነንት 3 ነጥብ 2) የተሰኘ መርኃ ግብር ተጀመረ።  

መርኃ ግብሩ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ በዓለም ባንክና በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በትብብር የተዘጋጀ ነው ተብሏል። 

በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የዓለም ባንክ፣ የባንክና ፋይናንስ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ጌታቸው ዋቄ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ መርኃ ግብሩ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ቅንጅት የሚተገበር ነው። 

መርኃ ግብሩ በዋናነት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ባልሆኑ አካባቢዎች የኃይል ተደራሽነት እንዲኖር ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ደግሞ ሌላኛው ትኩረቱ ነው ብለዋል። 

በ42 ሚሊየን ዶላር የሚካሄደው ይኸው መርኃ ግብር ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል። 

መርኃ ግብሩ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር ከ2021 ሲተገበር የቆየው ያልተማከለ የኤሌክትሪክ ኃይልና መብራት አቅርቦት ፕሮጀክት አካል ነው ተብሏል።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም