የአፍሪካ ሀገራት በጉምሩክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባቸው ተጠቆመ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ሀገራት በጉምሩክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባቸው ተጠቆመ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2016(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት በጉምሩክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር በማጠናከር ለአህጉራዊ ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባቸው ተጠቆመ።
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሊደርሽፕ ድርጅት ጋር በመተባበር በአፍሪካ የንግድ ሰንሰለትና የጉምሩክ አሰራር ላይ ያተኮረ ውይይት የሀገራት የዘርፉ ተወካዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር አዳዲስ አሰራሮች እየተተገበሩ ነው።
ኢትዮጵያ የተጠናከረ ህጋዊ የንግድ ስርዓትና የጉምሩክ አሰራርን ከማዘመን ባለፈ ከሌሎች ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
ከተለያዩ ሀገራት የተወከሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፥ እንደ አህጉር የጉምሩክ ግብረኃይል በማቋቋም ለህጋዊ ንግድ ትስስርና ለጉምሩክ አሰራር መዳበር በትብብር መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።
በመድረኩ በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ጉምሩክ ዘርፍ የሀገራት ተሞክሮዎች ቀርበዋል።