የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኢፍጧር መርኃ ግብር አካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኢፍጧር መርኃ ግብር አካሄደ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኢፍጧር መርኃ ግብር በአዲስ አበባ አካሄደ።
በመርኃ ግብሩ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር)፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የኢትዮጵያ ኃማኖቶች ጉባኤ ተወካዮች፣ የአዲስ አበባና የክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወካዮች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ጊዜ በረመዷን ወቅት መጠያየቅና መቀራረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ ያዘጋጀው የኢፍጧር መርኃ ግብርም ይህንን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዷን ወር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የተጣላን በማስታረቅና ሌሎች መልካም ተግባራትን በመከወን ማሳለፍ እንደሚገባው ተናግረዋል።