የሃይማኖት አባቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የሃይማኖት አባቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2016(ኢዜአ)፦ የሃይማኖት አባቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች መቀጠላቸውን ጠቅሰዋል።
ዛሬም ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተጉዘው በስብሰባው የተገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶችን ተቀብለን ተወያይተናል ብለዋል።