ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበረከቱ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበረከቱ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል።
በሽልማቱ የከበሩት ተቋማት የግብርና ሚኒስቴር/በስንዴ ልማት ፕሮግራም/፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተቋማቱ የኢትዮጵያ የእድገት እና የፈጠራ ልክ ማሳያ የሆኑ ምልክቶች ናቸው።