የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3/2016 (ኢዜአ)፡- ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ፡፡
ጎብኝዎቹም የዓድዋ ድል መታሰቢያ ታሪኩን፣ ጀግንነቱን እና ጽናቱን በሚመጥን መልኩ ታሪክን ያሸጋገረ፣ ትውልድ የሚማርበት እና በወቅቱ የነበረውን አንድነት በሚገልጽ መልኩ መገንባቱ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡