ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ሴቶችና ልጃገረዶችን ለመደገፍ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2016 (ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ-ሕዝብ ፈንድ እና የጃፓኑ ኢቶቻሁ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የሚገኙ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን መደገፍ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደረጉ።

የመንግስታቱ ድርጅት የስነ-ሕዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ኮፍ ኩዩሜ እና የኢቶቻሁ ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አኪኮ ሺኖዳ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የአጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።

በፕሮጀክቱም የሴቶችና ልጃገረዶችን የንፅህና አጠባበቅ እንዲሁም የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል የሚያስችሉ ድጋፍና እገዛዎች የሚደረጉ ይሆናል።

በገቢ ማስገኛ ተግባራት ላይ እንዲሰማሩ የማበረታታት እንዲሁም የንግድና የሙያ ክህሎት ስልጠናዎችም የሚሰጡ መሆኑ ተገልጿል።

በቤተሰብ ምጣኔ፣ በስነ-ተዋልዶ ጤና እና ሌሎችም ላይ እገዛና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም