ቀጥታ፡

የኢትዮ-ማልታ የመጀመሪያው ቢዝነስ ፎረም መካሄድ ጀመረ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮ-ማልታ የመጀመሪያው ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

የቢዝነስ ፎረሙ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና ማልታ ትሬድ በጋራ በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሃና አርዓያሥላሴ፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና የማልታ ትሬድ ኃላፊዎች እና ሌሎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ከማልታ ትሬድ የመጡ በማኑፋክቸሪንግ፣ ቱሪዝም፣ ንግድ፣ አይ ሲቲ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ጤና፣ ትምህርት እና ሌሎች የሥራ መስኮች ላይ የተሰማሩ የቢዝነስ ልዑካን  ቡድን አባላት የተካተቱ መሆኑ ተገልጿል።

ፎረሙ በኢትዮጵያና በማልታ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮች ለማስተዋወቅ ፎረሙ እንደሚያግዝም ነው የተገለፀው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም