ቀጥታ፡

16ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2016(ኢዜአ)፦ 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በነገው እለት እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ ጉባኤውን ከጠዋቱ ሶስት ስዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድም ተመላክቷል።

በዕለቱም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞች ሹመትን፣ የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እና የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን እና የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች እንደሚመራም ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም