ለዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም መሳካት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል- አቶ ተመስገን ጥሩነህ

374

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2016(ኢዜአ)፦ለዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም መሳካት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እስከ አሁን የደረሰበትን ደረጃ፣ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፣ የወደፊት ዕቅዶችና የስራውን ሒደት በተቋሙ ተገኝተው ጎብኝተዋል።


 

ብሔራዊ መታወቂያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራተጂ ውስጥ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አስቻይ ሁኔታ ተብለው ከተቀመጡ ስትራተጂዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዲጂታል መታወቂያ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና አገልግሎት የማግኘት ቅልጥፍናን ለማረገጥ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ መሆን ለእያንዳንዱ ዜጋ አስፈላጊ በመሆኑም ለፕሮግራሙ መሳካት መንግስት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም