ቀጥታ፡

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2016(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርጓል። 

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አባተ ምትኩ በዚሁ ጊዜ  እንደገለጹት፤ ድርጅቱ 500 ሺህ ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ። 


 

በተጨማሪም 500 ሺህ ብር ደግሞ ማዕከሉ ለሚያስገነባው ሕንጻው ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። 

ተቋሙ ድጋፉን ያደረገው ማዕከሉ የሚሰራውን ሥራዎች ለማገዝ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ድርጅቱ   ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። 


 

የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ፤ ተቋሙ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም