የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሰራን እንገኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሰራን እንገኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2016(ኢዜአ)፦ የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሰራን እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ የሚያሰራቸውን የ5ሺህ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ ማስጀመራቸውን ጠቅሰዋል።
እንዲሁም ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማሕበር፣ መንግስት ከስድስት ዓመታት በፊት በነጻ ባስረከበው 3 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባቸውን 5ሺህ ቤቶች መመረቃቸውንም ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የህዝቡን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል አንዱ አማራጭ የግል አልሚዎችን ማበረታታትና በአጋርነት የሚሰራበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሰራን እንገኛለን ሲሉም ገልጸዋል።