የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ አመራሮችና አባላት የእውቅናና ሽልማት መርኃ ግብር እያካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ አመራሮችና አባላት የእውቅናና ሽልማት መርኃ ግብር እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ ፖሊሳዊ ግዳጆች የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ አመራሮችና አባላት የእውቅናና የሽልማት መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።
እውቅናና ሽልማቱ ፖሊሳዊ ግዳጆችን በአገር ፍቅር ስሜትና ጀግንነት ለተወጡ አመራሮችና አባላት እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመርኃ ግብሩ የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ኮሚሽነር፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ በዚሁ ጊዜ፤ የፌዴራል ፖሊስ የተሰጠውን አገራዊ ግዳጅ በጀግንነት እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
ሕገ-መንግሥቱ ለዜጎች የሰጠው መብት እንዳይሸራረፍ ፖሊስ አበክሮ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው የዜጎች ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥም ፖሊስ ኃላፊነቱን በጀግንነት እየተወጣ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የመሆን ራዕይን አንግቦ እየሰራ መሆኑንም ገልጸው ለዚህም ዘመኑን በዋጁ ትጥቆች፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም በሰለጠነ የሰው ኃይል መደራጀቱን ቀጥሏል ነው ያሉት።
በዚህም የፖሊስ የማድረግ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን አመላክተዋል።