ዓለም አቀፋ ሴቶች ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በአድዋ መታሰቢያ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2016(ኢዜአ)፦አለምአቀፋ የሴቶች ቀን "ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ " በሚል መሪ ኃሳብ በአገር አቀፍ ደረጃ በአድዋ መታሰቢያ እየተከበረ ነው። 

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ለ113ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም በመከበር ላይ ይገኛል። 

እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ክልሎችና ከአዲስ አበባ ከተማ የተወጣጡ ሴቶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሴቶች አመራርነት ከየት ወደ የት እንዲሁም በሰላም እሴት ግንባታ ላይ የሴቶች ሚና በሚሉ ርዕሶች ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል። 

ዕለቱን ምክንያት በማድረግም ቀደም ብሎ በተጀመረው ንቅናቄ ለችግር ተጋላጭ ወገኖች የአልባሳት፣ የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል። 

ዕለቱን ከማክበር ባለፈም ለማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ጾታዊ ጥቃት ለተጋለጡ ሴቶች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል። 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም