የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤የካቲት 28/216 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ይጀምራሉ።በዛሬው መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከሻሸመኔ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት እንዲሁም መቻል ከባህር ዳር ከተማ ከምሽቱ 1 ሰዓት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሀዋሳ ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲያሸንፍ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል።

ክለቡ በ19 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ተጋጣሚው ሻሸመኔ ከተማ በበኩሉ ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በሁለቱ ሲሸነፍ በሁለቱ ነጥብ ተጋርቷል።

ሻሸመኔ ከተማ በ12 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌላኛው የ17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከባህር ዳር ከተማ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

መቻል ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በሁለቱ ድል ሲቀናው በሁለቱ ሽንፈት አስተናግዷል። አንድ ጊዜ አቻ ወጥቷል።

በ33 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአንጻሩ ባህር ዳር ከተማ ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ነው። በሶስቱ ሲሸነፍ አንድ ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል።

ባህር ዳር በ23 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገም ሲቀጥሉ አዳማ ከተማ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 10 ሰዓት፤ ሲዳማ ቡና ከ ወልቂጤ ከተማ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የፕሪሚየር ሊጉ የ17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሪሚየር ሊጉን በ35 ነጥብ እየመራ ይገኛል።

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም