ኢትዮጵያ በአለም የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በአለም የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች
አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በሩሲያ ሶቺ ከተማ እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
ፌስቲቫሉ መጭውን ግዜ አብረን እንጀምር በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በፌስቲቫሉ ላይ ከ100 ሀገራት የተወጣጡ ከ20ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሳተፋ ይገኛል፡፡
የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዳኤታ ሙና አህመድ እንደገለጹት በፌስቲቫሉ 70 አባላትን ያካተተ የኢትዮጵያ ልኡክ ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
መድረኩ ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲያስተዋውቁ እና እርስ በእርስ ልምድና ተሞክሯቸውን እንዲለዋወጡ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን የቡና ስርዓትን ጨምሮ ሌሎች እሴቶችን ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል ፡፡
ፌስቲቫሉ ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ 7 ቀን 2024 ድረስ የሚቆይ መሆኑ የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡