ቀጥታ፡

በበርሊን ጀርመን የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2016 (ኢዜአ)፦ በየአመቱ በበርሊን ጀርመን የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን (ITB) ተጀምሯል::

ይህ ኤግዚቢሽን በመላው ዓለም የሚገኙ ስመጥር የቱሪዝም ካምፓኒዎች እና ሀገራት ያላቸውን መዳረሻ እና የቱሪዝም አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው።

የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝተው ኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናውነቻቸው ያሉ የመዳረሻ ልማቶች እና የቱሪስት መስህቦችን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋርም በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ኤግዚብሽን ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ የሀገር ውስጥ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም