"ዓለም አቀፋዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዳደር ስርዓት ጅምሮች እና የኢትዮጵያ ትልም"  ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ነው

349

አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2016 (ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፋዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዳደር ስርዓት ጅምሮች እና የኢትዮጵያ ትልም" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የፖሊሲ ምክክር እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ይሽሩን ዓለማየሁ፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ተገኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ  መዳበር የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።


 

በዚህም በዘርፉ ችግር ፈቺ የሆኑ ሀሳቦችን እያመነጨ መሆኑን ጠቅሰው፥ የዛሬው የውይይት መድረክም የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

የመድረኩ ዓላማም የሰው ሰራሽ አስተውሎት በውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ተልእኮ ላይ ያለውን ጠቀሜታ እና ተጽእኖ ማስገንዘብ መሆኑን ገልጸዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት በየጊዜው እያደገ መሆኑ ስጋትንም ይዞ መምጣቱን ጠቅሰው ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ በዘርፉ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባት ጠቁመዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም