የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል ሽግግር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

200

አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2016(ኢዜአ)፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ጋር ያዘጋጁት የሳይበር ደህንነትና ዲጂታል ሽግግር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ሀገራዊ የሳይበር ሥነ-ምህዳር ማጠናከር ላይ በስፋት እንደሚመከርበት ተጠቁሟል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የሳይበር ደህንነት፣ የሳይበር ህግ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከ12 በላይ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

ጉባኤው ማህበረሰቡ ስለ ሳይበር ደህንነት ግንዛቤ እንዲኖረው የማድረግ ዓላማ እንዳለውም ተጠቁሟል።

በጉባኤው የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ፣ የኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃኑ በየነን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የዘርፉ አመራሮችና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም