የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል ሽግግር ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ ይጀመራል 

156

 አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ጋር  የሚያዘጋጁት  ሁለተኛው የሳይበር ደህንነትና ዲጂታል ሽግግር ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ ይጀመራል።

ሁለቱ ተቋማት በሰጡት መግለጫ፥  ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ የሳይበር ደህንነት፣ የሳይበር ህግ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ብለዋል።

ጉባኤው ማህበረሰቡ ስለሳይበር ደህንነት ግንዛቤ እንዲኖረው የማድረግ ዓላማ እንዳለውም ገልጸዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ማህበረሰቡ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የተሻለ አረዳድ እንዲኖረው እየሰራ ስለመሆኑም ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም