ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ናቸው - አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ከመሆናቸው ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዝርጋታ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ የተመራው ልዑክ በጂቡቲ የገዢው ፓርቲ 45ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።


 

በመርሃ-ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ የአጋርነት ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለገዢው ፓርቲ እና ለጂቡቲ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ከመሆናቸው ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዝርጋታ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል።


 

የብልጽግና ፓርቲ ለጂቡቲ ገዢው ፓርቲ ያለውን አብሮነት እና ወንድማማችነት ለማስቀጠል ያለውን ቁርጠኛ አቋምም ገልጸዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የቻይና፣ የኬንያ እና የሩዋንዳ ልዑካን መገኘታቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም