የአድዋ ድል በዓል በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
የአድዋ ድል በዓል በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተከበረ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2016(ኢዜአ)፦ 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በዓሉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የአሜሪካ እና ጀርመን ኤምባሲዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ጄዳ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል።
በስነስርዓቱም የሀይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።