ቀጥታ፡

128ኛው የአድዋ ድል በዓል በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከበረ

አዲስ አበባ፤የካቲት 23/2016 (ኢዜአ)፦128ኛው  የአድዋ ድል በዓል በጂቡቲ የሚገኙው ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ተከብሯል።

በጂቡቲ ያሉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት የሀይማኖት አባቶች እና ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል።

የሚሲዮኑ ምክትል መሪ አቶ ከበደ አበራ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው የጥቁር ህዝቦችም ድል በመሆኑ ይህን ታሪክ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ኃላፊነት ነው።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታየው አንድነት በሌሎች ሃገራዊ ስራዎች ላይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም