የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት  ለ128ኛ ዓመት የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ

108

 አዲስ አበባ የካቲት 22/2016 (ኢዜአ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት  ለ128ኛ ዓመት የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል።

 ክልልሉ ባስተላለፈው መልእክትም የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማሕተም፤ የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ተጋድሎ አርማ ና  አድዋ በሰው ልጆች ታሪክ በዓለም ላይ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ፤ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል  መሆኑን ጠቅሷል።

መላ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው አገራዊ ክብርንና ነጻነትን አስቀድመው በጋራ ዓላማቸው ላይ ከልብ የመግባት ውጤት መሆኑን አንስቷል።

ጀግኖች አባቶቻችን በሀገር ፍቅር ስሜት ለክብርና ነጻነት ሲሉ የደም፣ የአካል ዋጋ ከፍለው ዳር ደንበሯ የተከበረ፤ ነጻነቷ የተረጋገጠ ሀገር ለትውልድ አስረክበዋልም ብሏል።

የዛሬው ትውልድም ከአባቶቹ የወረሰውን የአንድነት፣ የመተሳሰብና ትብብር ስነልቦና ሰንቆ ሰላሟ የጸና በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ላይ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ሒደት አርበኛ ሊሆን ይገባል ሲልም መልእክት አስተሏልፏል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም