የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት፣ አምራቾችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ::
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እንዳሉት፤ የንቅናቄው ዋና አላማ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት ነው።
ባለፉት ዓመታት በተካሔደው ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አልባሳትን፣ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶችን በስፋት በማምረት ውጤት መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ኢኮኖሚውን በማነቃቃትና በስራ እድል ፈጠራም ከፍተኛ አስተዋፅዖኦ ማበርከቱን አቶ መላኩ ተናግረዋል፡
በዘንድሮው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የአገር ውስጥ የገበያ መዳረሻውን በማስፋትና አሁን ያለውን የስራ እድል ማሳደግ ላይ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ታምራት ንቅናቄ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ መደረጉ ይታወቃል::